አምስቱ አዕማደ ምስጢር
THE FIVE PILLARS OF OUR FAITH


አዕማደ ምስጢርን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
Why is it Important to Know the Pillars of Our Faith?

በሥጋዊ ዐይን እግዚአብሔርን ማየትና በውስን አዕምሮ ሐልዎተ እግዚአብሔርን መመርመር አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ ስለራሱም ይሁን ለእርሱ አንክሮና ተዘክሮ ስለተፈጠሩት ፍጥረታት ገና ያልደረሰባቸው ነገሮች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን እርሱ በወደደው መጠን ለአባቶቻችን ለቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት አዕምሮአቸው ሊረዳው በሚችለው መጠን በብዙ ምሳሌና በብዙ ጎዳና ማንነቱን ገልጾላቸዋል (ዕብ 1፡1-2)፡፡ እግዚአብሔርንም የምናውቀው እርሱ ራሱን ለሰው ልጆች በገለጠው መጠንና የሰው ልጅ መረዳት በሚችለው መጠን ብቻ ነው፡፡

It is not possible to see God with physical eyes and examine God with your limited mind. Because there are things that the human being has not yet reached, whether it is about himself or about the creatures that were created for him. But God, as much as He pleased, revealed Himself to our forefathers, the holy prophets and apostles in many ways and in many ways, as much as their minds could understand (Hebrews 1:1-2). We know God only to the extent that He has revealed Himself to mankind and to the extent that mankind is able to understand.

አንድ ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር አምስቱን አዕማደ ምስጢራት በሚገባ ከተማረ በሕይወቱ ምንም እንኳን ነፋሳት ቢነፍሱ ጎርፍም ቢጎርፍ ከእምነቱ ምንም ሊያናውጠው አይችልም፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ከደሙና ከአጥንቱ ተዋሕደው የዚህን ዓለም ፈተና እንዲቋቋም ያስችሉታል፡፡ አዕማደ ምስጢራትን ያወቀና ያመነ እና የሥላሴ ልጅነትን በጥምቀት ያገኘ አባት እናት ቢሞቱበት በሥላሴ አባትነት ይጽናናል፡፡ መከራ ቢደርስበት አምላክ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ላይ የደረሰበትን መከራ እያሰበ ከምንም አይቆጥረውም፡፡ ረኀበ ነፍስ ቢደርስበት ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፤ ክቡር ደሙንም ይጠጣል፡፡ በእምነቱ ምክንያት እንገድልሀለን ቢሉት ትንሣኤ ዘጉባዔን (ትንሣኤ ሙታንን) ተስፋ ያደርጋል፡፡ ይህም በመሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከኅሊና እግዚአብሔር እንዳይርቅና ከእግዚአብሔር ጋር በእምነት እንዲጸና እነዚህን ምሰሶዎች (ምስጢራት) ታስጨብጠዋለች፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች (ምስጢራት) የተደገፈ ጠላቶቹን አጋንንትንና መናፍቃንን ድል ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ አዕማደ ምስጢራትን በሚገባ ማወቅ ሃይማኖትን በሚገባ ለመረዳት፣ ከጥርጥርና ከኑፋቄ ለመጠበቅና በሃይማኖት ጸንቶ ጽድቅን ለመፈጸም ይጠቅማል፡፡

If a person has thoroughly learned the Five Pillars of Faith while living in this world, nothing can shake him/her from their faith, even through the storms and strong winds of life. These teachings, when embedded deep within one, enable one to withstand the trials of this world. When undergoing the many trials and tribulations of this world, the believer will gain solace knowing the great trials that God Incarnate endured while He was on Earth.

If his/her soul hungers, they will partake in the Body and Blood of Christ. If his/her life is threatened due to his faith, they will be comforted by the knowledge of the rising of the dead. Accordingly, the Holy Church teaches her followers these Pillars (Mysteries) so that they do not stray away from God and to strengthen their bond to their faith. Supported by these Pillars (Mysteries), the believer will successfully defeat the forces of evil and heretics. Knowing the Pillars of Faith is instrumental in deepening the believer’s understanding of the Ethiopian Orthodox Tewahedo faith and to guard against doubts, and to stand firm on faith and eventually attain righteousness.

1. ምሥጢረ ሥላሴ
Mystery of The Trinity


ሠለሰ ሦስት አደረገ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፤ ሥላሴ ማለት ሦስትነት ማለት ነው ። ምሥጢረ ሥላሴ ስንልም የአምላክን አንድነት እና ሦስትነት ማለታችን ነው።

ሥላሴ በስም፤ በአካል፤ በግብር ሦስት ናቸው ብንልም በመለኮት፤ በህልውና፤ በባሕርይ፤ በእዘዝ በአገዛዝ በመሳሰሉት አንድ ስለሆኑ አንድ አምላክ ተብሎ ይታመናል ይጠራል እንጅ ሦስት አማልክት አይባልም። ከዚህም የተነሣ ሥላሴ ሦስት ሲሆኑ አንድ፤ አንድ ሲሆኑ ሦስት በመሆናቸው ምሥጢር ተባለ። ይህም ለሚያምን ብቻ የሚገለጽ ምሥጢር ነዉ።

  • በሥም፡- አብ፣ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ” (ማቴ. ፳፰፡፲፱)
  • በግብር፡- አብወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ ነው።” (ዮሐ. ፲፬፡፳፭)
  • በአካል፡- ለአብፍጹም አካል፣ ለወልድ ፍጹም አካል፣ ለመንፈስ ቅዱስ ፍጹም አካል አለው” (ማቴ. ፫፡፲፮)

የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት የጀመረው እራሱ እግዚአብሔር ነው።

መጀመሪያ አዳምን ሲፈጥረው ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሣሌያችን ብሏል (ዘፍ. ፩ ፳፮)። እነሆ በዚህ አንቀጽ “እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሣሌያችን” የሚለው ንግግር የሁለት የሦስት ተናጋሪዎች እንጂ የአንድ ተናጋሪ ቃል አይደለም። በመቀጠል “እግዚአብሔር አምላክም አለ እነሆ አዳም ከኛ እንደ አንዱ ሆነ” (ዘፍጥረት ፫፡፳፪)። ስለዚህ እግዚአብሔር ከኛ እንደ አንዱ ሆነ በማለቱ ሦስትነቱን ያስረዳል።

እግዚአብሔርም አለ “ኑ እንውረድ ቋንቋቸውንም እንደባልቀው አንዱ የባልንጀራውን ነገር እንዳይሰማ” ብሏልና። (ዘፍጥረት ፲፩፡፯) እነሆ በዚህ አንቀጽ እግዚአብሔር “ኑ እንውረድ” ብሎ በመናገሩ ከሁለትነት የተለየ ሦስትነትን ያስረዳል። መረጃውም ሦስት ተናጋሪዎች በአንድ ቦታ ሆነው ሲነጋገሩ ሦስተኛው ሁለቱን “ኑ እንውረድ” ሊላቸዉ ይችላል። ሁለት ሆነው ግን አንዱ ሁለተኛውን “ና እንውረድ” እንጂ “ኑ እንውረድ” ሊለዉ ስለማይችል ነዉ።

ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የእግዚአብሔር ቃላት ተገልጸው ሲተረጎሙ አካላዊ ልባቻው አብ፤ አካላዊ ቃሉ ወልድ እና አካላዊ ሕይወቱ (እስትንፋሱ) መንፈስ ቅዱስን ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ብሎ እንዳነጋገራቸዉ ይታወቃል።

የእግዚአብሔር የአንድነቱ እና የሦስትነቱ ማስረጃ ሁነው የታመኑ እነዚህ ሦስት ቃላት ከአንድ የበዙ ተናጋሪዎች ቃላት መሆናቸው ይታወቃል። መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህም በሌላ አንቀጽ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን አይቶት እንዲህ ይላል፦ “ዖዝያን ንጉሥ በሞተበት ዓመት እኔ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ በረጅም ዙፋን ተቀምጦ አየሁት፤ ሱራፌልም ከርሱ በላይ ቁመው ነበር። አንዱም ለአንዱ እንዲህ ሲሉ ይጮኹ ነበር፦ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ ምድር ሁሉ ምስጋናውን ሞልታለች (ኢሳ. ፮፡፩-፫)።

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸውም” ሲል ራሱን አብን እና መንፈስ ቅዱስን በመግለጽ ከሦስት አካላት ያልበለጠ ከአንድ አካልነት የወጣ ከሦስት አካላት ያልበዛ ሦስት ብቻ መሆኑን አስረድቷል። (ዮሐ. ፲፭፡፳፮፤ ማቴ. ፳፰፡፲፱)።

The word "Trinity" indicates the three persons of the one and the only God, namely the Father, the Son, and the Holy Spirit. The Father the Son and the Holy Spirit are one in nature, essence, divinity, will, but three in name and in person. The Father has begotten the Son, the Son is begotten from the Father, and the Holly Spirit proceeds only from the Father. The Father can't be called the Son, or the Holy Spirit, the Son can't be called the Father or the Holy Spirit, and the Holy Spirit can't be called the Father or the Son. Even though the Son is begotten from the Father, and the Holy Spirit proceeds from the Father, there was no time when the Father was without the Son and the Holy Spirit, the Son without the Father and the Holy Spirit, or the Holy Spirit without the Father and the Son. They are equal in precedence and are one in Godhead. Thus we do not say three Gods, but three persons, one God.

In the Old Testament, we see that there is more than one person of the one and only God. This is evident in the following passages:

  • "Let Us make man in Our own image, according to Our likeness" Genesis 1:26
  • And the Lord said "… Come let Us go down and there confuse their language …" Genesis 11:6-7

In the above passages we know that there is more than one person because of the reference "… let Us …", but we also know that there is only one Lord and God, because it says "the Lord said …".

The three persons was first revealed in the scripture when the Holy Trinity appeared to Abraham as three guests. "So he lifted his eyes and behold three men were standing by him; and when he saw Them, he ran from the tent door to meet them, and bowed himself to the ground and said, "My Lord, if I have now found favor in Your sight, do not pass on by Your servant". (Genesis 18:1-3). Even though he saw three persons, he said "My Lord" and not "My Lords" because the three persons he saw are one in Godhead and Lordship. Moses also wrote on Genesis 18:1, "The Lord appeared to him …" insted of "the Lords …" because the Lord God is one, but revealed to Abraham in His three persons. It is to the Trinity that the Angels sing "Holy, Holy, Holy" when worshiping God, but testify to His oneness by saying "Holy, Holy, Holy is the Lord of hosts; the whole earth is full of His Glory" (Isaiah 6:3).

The three persons of God is also revealed in the New Testament, when John baptized Jesus Christ. "When He had been baptized Jesus came up immediately from the water; and behold, the heavens were opened to Him, and He saw the Spirit of God descending like a dove and alighting upon Him. And suddenly a voice came from heaven, saying, “This is My beloved Son, in whom I am well pleased." Jesus Christ, the incarnate God the Son, the Holy Spirit descending like a dove, and God the Father speaking from heaven testifying about Jesus Christ is clear evidence to the three persons of God, the Father, Son and Holy Spirit.

2. ምሥጢረ ሥጋዌ
MYSTERY OF INCARNATION


"ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ"   (ዮሐ፥ ፩፡፲፬)

"የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ" (ገላ፥ ፬፣፬)

ሐዋርያት እንዳስተማሩን በከዊን ሥሙ ቃል የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል ማርያም ሰው እንደሆነ እናምናለን። ሰው ሆነ ማለትም የሰውን ጠባያት ነፍስን ሥጋን በረቂቅ ባሕርዩ ለበሰ ተዋሐደ ማለት ነው። ዓለም ሳይፈጠር ጥንት ሳይኖረው ከአብ ከአካሉ፣ ባሕርዩ ከባሕርዩ የተገኘ አካላዊ ቃል ዓለም ከተፈጠረ በኋላ ኑሮ ከድንግል ማርያም የተከፈለ /የተገኘ/ ሥጋና ነፍስን ሆነ፤ ከድንግል ማርያም የተከፈለ /የተገኘ/ ሥጋና ነፍስ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ የተገኘ አካላዊ ቃል ሆነ። ቃል ሥጋ ሆነ  (ዮሐ፥ ፩፡፲፬)

ቃል ሥጋ ሆነ ሲባል መሆን የሁለቱ ነውና ሥጋ ቃልን ሆነ ማለት እንዳለበት ማስተዋል ይገባናል። ቃል የሚባለው መለኮትነቱ ነው፣ ሥጋ የሚባለው ትስብእቱ ነው ትስብእትም ማለት ሰው መሆን ሰውነት ማለት ነው። ምሥጢሩ ሲገለጥ ነፍስና ሥጋ ማለት ነው፤ ቃል ሥጋ ሆነ ማለት በጉልህ ሲነገር ቃል ከሥጋ ጋር ፣ ሥጋ ከቃል ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ ማለት ነው። ሃይማኖታችንን ተዋሕዶ ማለታችንም ይህን ይዘን ነው።

ቃል ሥጋ ሆነ ያለው ቃል የሎጥ ሚስት የጨው ድንጋይ ሆነች እንዳለው እና  ውኃ ወይን ሆነ እንዳለው ሁኔታ አይተረጎምም  (ዘፍ፥ ፲፱፡፳፮፤  ዮሐ፡ ፪፡፱)  የሎጥ ሚስት ሰው ሳለች ጨውነት አልነበራትም የጨው ድንጋይ ስትሆን ከሰውነት ወደ ጨውነት ተለውጣለች። የቃና ውሃም ከወንዙ ሲቀዱት ወይንነት አልነበረውም ጌታ ወይን ሲያደርገው ከውኃነት ወደ ወይንነት ተለውጧል። አካላዊ ቃል ግን ሥጋ ሆነ ሲባል ከባሕርዩ ማለት ከቃልነቱ፣ ከመለኮትነቱ ሳይለወጥ ነፍስን ሥጋን ተዋሐደ ማለት ነው። መለኮቱ አልተለወጠም እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም!

ሰው ሲሆን ከባሕርዩ አለመለወጡንም የራሱ ትምህርት ያስረዳናል፦ "ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም ከሰማይ ከወረደው በቀር እርሱም የሰው ልጅ በሰማይ የሚኖር" ዮሐ፥ ፫፡፲፫ "እኔና አብ አንድ ነን"( ዮሐ፥ ፲፡፴) "እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ" ብሏልና (ዮሐ፥ ፲፬፡፲፩)

ቃል ሥጋ ሲሆን ከቃልነቱ፣ ከመለኮትነቱ ተለውጦ ሥጋን ቢሆን ኑሮ በሰማይ መኖር አይቻለውም፣ እርሱም በምድር ሳለ እራሱን በሰማይ የሚኖር ባላለም ነበር። እንደ እውነቱ ግን ቃል ሰው ሲሆን ከመለኮትነቱ አልተለወጠምና በሰውነቱ በምድር ሳለ በመለኮትነቱ በሰማይ ነበር። ስለዚህም በምድር እየታየ በሰማይ የሚኖር አለ። ዳግመኛም ከመለኮትነቱ ተለውጦ ቢሆን ከሴቶች ከአንዲቱ ከማርያም የተወለደ አንድ ሰው ሲሆን ከእግዚአብሔር ከአብ ጋር መተካከልና በአብ እንደ እውነቱ ግን ሰው ሲሆን ከቃልነቱ አልተለወጠምና በመለኮትነቱ ከአብ ጋር ትክክል ነው በቃልነቱም በአብ ባሕርይ አለ ከአብ አይለይም።

ስለዚህ አንድ ሰው ሁኖ ሲታይ በሰውነቱ ቃል ሲናገር ሲሰማ ከመለኮትነቱ ስላልተለወጠ እኔና አብ አንድ ነን አለ ሥጋም ቃል ሲሆን ከባሕርዩ አልተለወጠም። ቃልን ሆነ ሲባል ከባሕርዩ ተለወጠ ማለት አይደለም። ከባሕርዩ ሳይለወጥ ቃልን ተዋሐደ ማለት ነው። ከሰውነት ባሕርዩ ቃል ወደ መሆን ተለውጦስ ቢሆን ኑሮ ሲወለድ በእጅ ባልተዳሰሰም ነበር በተወለደበትም ቦታ ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ ባልታየም ነበር። ከዚህም በሌላ ሁኔታ እንደ ወተትና እንደ ውኃ፣ እንደ ውኃና እንደ ማር የተበረዘ (የተቀላቀለ) አይደለም። ባሕርይ እና ባሕርይ ሳይጣፋ(ሳይበረዝ) እንደ ነፍስና እንደ ሥጋ አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ተዋሐደ እንጂ በተዋሕዶም መንታነት (ሁለትነት) የለበትም። በተወለደም ጊዜ በሰውነት ጠባይ ሥርዓት ከልደቱ እስከ ሦስት ዓመት የእናቱን ጡት በመጥባት፣ ከሦስት ዓመቱ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ እህል በመብላት በመጠጣት ሰውነቱን አጸና፤ በቁመቱም በየጥቂቱ አደገ። መጽሐፍ ቅዱስ "ኢየሱስም በጥበብና በቁመት ያድግ ነበር"(ሉቃ፥፪፡፶፪)  "በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም፤ ኃጢአትን አልሠራም ሐሰትም በአፉ አልተገኘበትም"  ኢሳ፥ ፴፫፡፱  "ልጅ እንደመሆኑ ለእናቱ ይታዘዝ ነበር" (ሉቃ፥ ፪፡፶፩)

Incarnation is the embodiment of God the Son to become perfectly human without changing, altering or lessening His divinity or Godhead. Christ is God the Son incarnate Who was born of the Virgin Mary for our salvation. He is one nature of two natures - divine and human. His divine and human nature were completely united at conception in the womb of the Virgin Mary, but without mingling, yet without separation. Therefore, we say that He is perfectly human and perfectly God. There was never a time when His divinity was separated from His humanity once the complete union took place at conception. This is a great mystery that words cannot explain, and is beyond the grasp of our wits. That is why the apostle Paul wrote "And without controversy, great is the mystery of godliness: God was manifested in the flesh, justified in spirit, seen by the angels, preached among the gentiles, believed on in the world, received up in Glory." (1Timothy 3:16).

God has often spoken about His incarnation through different prophets. The prophet Isaiah said, "For unto us a Child is born, unto us a Son is given; and the government will be upon His shoulder. And His name will be called Wonderful, Counselor, Mighty God, Everlasting Father, Prince of Peace" about Jesus Christ. The prophet Ezekiel also wrote "Then He brought me back to the outer gate of the sanctuary which faces toward the east, but it was shut. And the Lord said to me, “This gate shall be shut; it shall not be opened, and no man shall enter by it, because the Lord God of Israel has entered by it; therefore, it shall be shut", clearly indicating the birth of our Lord from the Virgin Mary. This revelation of Ezekiel is also a clear testimony of the perpetual virginity of our holy mother saint Mary. The prophet Isaiah wrote "behold a virgin shall conceive and bear a son and shall call his name Immanuel" (Isaiah 7:14) about the birth of Christ from the Virgin Mary.

John the apostle wrote in his gospel, "In the beginning was the Word, and the Word was with God, and the Word was God … And the Word became flesh and dwelt among us" (John 1:1 - 14). This is a clear indication of the incarnation of Christ, the Son of God, who is one in essence with God the Father, and the Holy Spirit. John said "the Word was with God", indicating the separate person of the Son, but said "the Word was God" because the Son is one in essence with the Father and the Holy Spirit. It is this incarnate Son of God Elizabeth called "… My Lord" and the baby in her womb leaped for (Luke 1:41-42).

3. ምሥጢረ ጥምቀት
MYSTERY OF BAPTISM


ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴ እና በምሥጢረ ሥጋዌ ለሚያምን ሁሉ የተሰጠ የኃጢአት መደምሰሻና ከእግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን መቀበያ ነው። ጥምቀት የኃጢአት መደምሰሻ እንደሚሆንም እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢያት ትንቢት አናግሯል።  ትንቢቱም የጠራ ውኃ አፈስስባችኋለሁ። (ሕዝ. ፴፮፡፳፭) ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል። (ሚክ. ፯፡፲፱)

ኃጢአታችንን መደምሰሻና ልጅነትን መቀበያችን ጥምቀት እንዲሆን ያደረገ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጥምቀት ያስተማረውን ትምህርትና ያዘዘውን ትዕዛዝ ቀጥለን የምንጠቅሰው ነው፦ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ እውነት እውነት እልኻለሁ ማንም ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባ ዘንድ አይችልም። (ዮሐ. ፫፡፭) እንግዲህ ሂዱና በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ አጥምቋቸውም። (ማቴ. ፳፰፡፲፱) ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። (ማር. ፲፮፡፲፮) ከእግዚአብሔር መወለዳችን የእግዚአብሔርን ርስት መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ነው።

መንግሥተ ሰማይን በጥምቀት እንጂ ያለ ጥምቀት ልንገባበት እንደማንችል ጌታችን በትምህርቱ እንደገለጸልን አውቀን መኖር ይገባናል። ይኽም የጌታ ትምህርት ስለ ጥምቀት ለነቢያት ትንቢት መፈጸሚያ፣ ለሐዋርያት ትምህርት መማሪያ ነው። የነቢያት ትምህርት በመጀመርያ የተጠቀሰ ነው። የሐዋርያት ትምህርት ቀጥሎ የምንገልጸው ነው፦ ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከተማሩ በኋላ ጥምቀት ኃጢአት ማስተስረያና የልጅነት መቀበያ መሆኑን ሲያስተምሩ እንዲህ ብለዋል፦ ጴጥሮስም አላቸው፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። (ሐዋ. ፪፡፴፰)

ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ (ኤፌ. ፭፡፳፭) ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም። (ቲቶ ፫፡፬-፭) የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ስለ ጥምቀት እንዲሁ ሲሉ አስተምረዋል፦ ኃጢአትን ለማስተስረይ በምንጠመቃት አንዲት ጥምቀትም እናምናለን። (ሃይ. አበው ዘሠለስቱ ምዕት) ጥምቀት የኃጢአት መደምሰሻና የእግዚአብሔርን ልጅነት ማግኛ መሆኑን ስናምን ለዚህ እምነታችን መሠረቱ ከብዙ በጥቂቱ የጠቀስነው የነቢያት ትንቢትና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት፣ የሐዋርያትና የሊቃውንትም ትምህርት ነው። የምንጠመቅበት ውኃም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ ጎን የፈሰሰ ውኃ ነው። ይኽን ውኃ የምናገኘው በጸሎት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው።  አጥማቂው ካህን በመጠመቂያ ውኃ ላይ መጽሐፈ ክርስትናን (ጸሎተ ክርስትናን) ይጸልይበታል፤ አሐዱ አብ ቅዱስ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎም በመስቀል ይባርከዋል። በዚህ ጸሎትና ቡራኬ የተጸለየበት ውኃ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተለውጦ ከጌታ ጎን የፈሰሰ ውኃ ሆኖ ይከብራል።

ሕፃናት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ወንዶች በአርባ ቀን ሴቶች በሰማንያ ቀን በጥምቀት ተወልደው ሁለተኛ ልጅነትን ያገኛሉ። አንዳንዶችም በተለያዩ ሁኔታዎች ሕፃን ሳሉ መጠመቅ ያልቻሉና እንዲሁም ደግሞ የክርስትና ሃይማኖትን ተምረው መጠመቅ የሚፈልጉ ወጣቶችና ዓዋቂዎች ሁኔታው በፈቀደበት ጊዜና የሃይማኖት ትምህርቱን እንደጨረሱ ይጠመቃሉ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት ሲከናወን በዚያው ዕለት ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ምሥጢራት ምሥጢረ ሜሮን እና ምሥጢረ ቁርባን ይፈጸማሉ።

ይኽ የጥምቀት ምሥጢር ከበደል ነጻ ወጥተን ሕይወትን የምንቀበልበት እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስን በሞቱ እና በትንሣኤው የምንመስልበት በመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች እና ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦ በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ በጥምቀት ደግሞ… ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። … ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ። በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። (ቆላ. ፪፡፲፪-፲፬) በማለት እና ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? (ሮሜ ፮፡፫) የጥምቀትን አስፈላጊነት አስተምሮናል።

Baptism is the sacrament by which we are reborn of the Holy Spirit to become children of God, a grace of childhood that was lost when Adam and Eve transgressed God's commandment (John 3:5, Rom 8:14). It is a great mystery for we receive the invisible gift of the spirit of childhood through visible sacramental rite. Our Lord Jesus Christ said, "The wind blows where it wishes, and you hear the sound of it, but cannot tell where it comes from and where it goes. So is everyone who is born of the Spirit." indicating the invisible grace we receive through baptism. (John 3:8).

Through baptism we become one with Christ, and are united in his death and resurrection. The apostle Paul explains this by saying, "Do you know that as many of us were baptized into Christ Jesus were baptized into his death? Therefore, we were buried with Him through baptism into death, that just as Christ was raised from the dead by the glory of the Father, even so we also should walk in newness of life" (Rom. 6:3).

We have to receive the sacrament of baptism to inherit the kingdom of God. This is indicated by Christ's word to Nicodemus: "Most assuredly I say to you, unless one is born again, he cannot see the kingdom of God. Unless one is born of water and the spirit, he cannot enter the kingdom of God." (John 3:3-5). Therefore, males are baptized at 40th day after birth and females at the 80th day after birth in the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, according to Christ's commandment to His apostles (Math. 28:19).

The water with which we are baptized is not merely water like the one John the Baptist was baptizing with, but divine. John the Baptist said, "I indeed baptize you with water unto repentance, but He who is coming after me is mightier than I, whose sandals I am not worthy to carry. He will baptize you with the Holy Spirit, and fire." These words testify that Christ has given us the grace of baptism with the invisible fire of the Holy Spirit, through visible divine water (Math. 3:11). Therefore, we are baptized with water and the Holy Spirit to be rightfully called the children of God only once, for there is only one baptism (Eph. 4:5).

Our Lord Jesus Christ has taught us how to walk in the path of salvation to inherit his everlasting kingdom not just by words but also by setting examples. That is why He was baptized by John the Baptist, who was sent by the Lord Himself "to prepare the way of the Lord" (Math. 3:3). He was baptized to set an example for us, so that the prophecy may be fulfilled, and to reveal the three persons of God, the Father, the Son and the Holy Spirit (Mathew 3:16-17, Psalm 114:5).

Baptism is the first sacrament given to all who enter the Church. It is the door to the beginning of eternal life. That is why the apostle Peter wrote that Baptism saves us (1Pet. 3:21). As our path in life in this world starts at birth from our mother's womb, our path in salvation also starts with the second birth, which is baptism (John 3:3). That is why this sacrament is given freely to children, for salvation can be attained only through baptism. No one but Christ our Lord has chosen his birth mother. Since this is a rebirth, not into this world, but into an everlasting life, this sacrament should not be withheld from children. When the disciples rebuked the little children that were brought to Christ, He did not say, return them until they come of their own accord, but said, "Let the little children come to me, and do not forbid them" (Math 19:13). He also added, "For such is the kingdom of heaven" indicating that, it is not children who should be like adults, but adults who should be like children to inherit the kingdom of God.

Christ spoke the words, "He who believes and is baptized will be saved" for adults who come into the Christian faith from unbelieving (Mark 16:16). However, as we can see from Acts 16:15, if the family head believes, it is not only the head, but also the household who is baptized.

4. ምሥጢረ ቁርባን
MYSTERY OF COMMUNION


ቁርባን ምንድነው?

* ቁርባን የክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ነው (ኤፌ. ፭፥፪)

አምላካችን፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሥጋውና ደሙ እንዲህ ብሎ ነበር፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምምሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው። (ዮሐ. ፮፥ ፴፪–፴፫)
በመቀጠልም ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁቁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል (ዮሐ. ፮፥ ፶፭–፶፰)

ጌታችን ይህን ነገር በቃሉ ሲነግራቸው መጀመሪያ ለሰሙት ሰዎች በሥራ እስኪያሳያቸው ድረስ ሊታመን የማይችል ረቂቅ ነገር ነበር። ኋላ ግን ሠርቶ ባሳያቸው ጊዜ ተረድተው አምነውበታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ የሥጋውና የደሙን ምሥጢር ሲያሳይ እንዲህ ነበር ዓርብ ሊሰቀል ሐሙስ ማታ ማለት የሐሙስ ቀን አልፎ የዓርብ ማታ ሲገባ ዓልአዛር በተባለው ሰው ቤት ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መጀመሪያ የኦሪትን መሥዋዕት ሠውቶ በልቷል። ወዲያው የበሉትን የኦሪት መሥዋዕት በተአምራት ከሆዳቸው አጥፍቶ ሰዎች ለእራት ካመጡለት ኅብስት አንዱን አንሥቶ ያዘና ወደ አባቱ ጸለየ።

ኅብስቱንም በሥልጣኑ ለውጦ ሥጋውን አድርጎ ይህ ስለ እናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነውና እንኩ ብሉ ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው መታሰቢያዬንም ይህ አድርጉት ብሎም አስተማራቸው። ቀጥሎም ወይን በጽዋ ቀድቶ ያዘና ጸለየ ወይኑንም ለውጦ ደሙ አድርጎ ይህ ስለእናንተ የሚፈስ ደሜ ነው እንኩ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው (ሉቃ. ፳፪፥ ፲፱–፳ ማቴ. ፳፮፥ ፳፮ ማር. ፲፬፥ ፳፪)

ሳይሰቀል አስቀድሞ ምሥጢረ ቁርባንን ያሳየበት ምክንያት ዓርብ ዕለት በተሰቀለ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተገናኝቶ ሥራ ለመሥራት ስለማይቻል ነው (ዮሐ. ፲፮፥፳፪ )ሐዋርያትም መታሰቢያዬን ይህን አድርጉ ባላቸው ትምህርት መሠረት ኅብስትና ወይን አቅርበው በጸሎት ሥጋውንና ደሙን እያደረጉ ያቆርቡ ነበረ። (፩ኛቆሮ. ፲፥፲፮) ዛሬም በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሥጋውና ደሙ በቀሳውስት እጅ ይሰጠናል፤ የክርስቶስን ሥጋና ደም የምናገኝ በጸሎት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው።

የቤተ ክርስቲያን ማገልገያ ዕቃዎች ንዋየ ቅድሳት ይባላሉ በአማርኛም የክብር፣ የንጽሕና ዕቃዎች ማለት ነው፤ ከንዋየ ቅድሳትም ለሥጋውና ለደሙ ማቅረቢያና ማቀበያ የሆኑ ሦስት ንዋየተ ቅድሳት አሉ እነርሱም፦ ጻሕልና፣ ጽዋ፣ ዕርፈ መስቀል (ማንኪያ) ናቸው።

ስለዚህ ጌታችን እንዲህ ብሏል ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ ለእርሱ የዘለዓለም ሕይወት አለው እኔም በኋለኛው ቀን አሥነሳዋለሁ፤ ሥጋዬ የእውነት መብል ነውና፣ ደሜም የእውነት መጠጥ ነውና ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ አድራለሁ፤ የላከኝ አብ ሕያው እንደሆነ እኔም ስለ አብ ሕያው ነኝ የሚበላኝም ደግሞ እርሱ ስለ እኔ ሕያው ይሆናል። (ዮሐ. ፮፥፶፬ )

ሥጋውንና ደሙን መቀበልም እግዚአብሔርን ፈርቶ ከሠሩት ኃጢአት ተጸጽቶ ማረኝ ብሎ አልቅሶ ለወደፊቱም ከኃጢአት ተለይቶ ነው። (፩ኛ ቆሮ. ፲፩፥፳፰)

ያለፍርሃት በድፍረት ያለንጽሕና በኃጢአት ሆኖ ቢቀበሉት ማለት ከሟርት፣ ከስርቆት፣ ከዝሙት፣ ከሐሜት፣ ከፌዝና፣ ከቧልት ሳይለዩ ቢቀበሉት ግን የገሃነም ፍርድን ያመጣል እንጂ ከኃጢያት ፍርድ አያነፃም፤ (፩ኛ ቆሮ. ፲፩፥፳፯፤ ዕብ. ፲፥፳፱)

Communion is the act of receiving the Eucharist, the body of and blood of Jesus Christ, in liturgical worship. The belief that the body and wine, consecrated during liturgical worship, changes to be the body and blood of Jesus Christ, and that what we receive is the true body and blood of Jesus Christ is called the Mystery of Communion. The Mystery of Communion is the sacrament through which Jesus Christ dwells in us: “He that eats My flesh, and drinks My blood, dwells in Me, and I in him.” (John 6:56)

Jesus Christ instituted this Sacrament on the eve of His crucifixion, as we can see from the following passage from the gospel of Mathew: “And as they were eating, Jesus took bread, and blessed it, and brake it, and gave it to the disciples, and said, Take, eat; this is My body. And he took the cup, and gave thanks, and gave it to them, saying, Drink ye all of it; For this is My blood of the New Testament, which is shed for many for the remission of sins.” (Mathew 26:26-28). Christ commanded the disciples to do the same (Luke 22:19; 1 Corinthians 11:24-25).

Before Jesus Christ instituted the Eucharist, He has taught that whoever eats of His flesh, and drinks of His blood will inherit the kingdom of God: “I am the living bread which came down from heaven: if any man eat of this bread, he shall live forever: and the bread that I will give is My flesh, which I will give for the life of the world … Whoso eats My flesh, and drinks My blood, has eternal life” (John 6:51, 54). It is essential that we partake of this sacrament for salvation because He said, “Verily, verily, I say unto you, except ye eat the flesh of the Son of man, and drink his blood, ye have no life in you.” (John 6:53)

This is the reason that the Eucharist is the central element of Orthodox Worship. The offering of sin in the Old Testament was animal sacrifice. But in the New Testament, Christ gave us His own body and blood as a sacrifice to cleanses the body and the soul from sin. That is why John the Baptist testified, “Behold the Lamb of God, which takes away the sin of the world.” (John 1:29) John referred to Him as “the Lamb of God”, because He would be crucified on the cross for our salvation, and would give us His flesh and blood as a sacrifice of the New Testament. Accordingly, just as Christ blessed the bread and wine, and said, “This is my body … This is my flesh”, the bread and wine offerings change into His body and His blood with the blessing and the prayer of the priest in our liturgical worship. Therefore, we believe and confess that the bread and wine we receive is truly the body and blood of Jesus Christ, God the Son incarnate.

We have to receive the Eucharist with such faith, for it brings condemnation instead of salvation if we receive it without faith. The apostle Paul attests when he says, “whosoever shall eat this bread, and drink this cup of the Lord, unworthily, shall be guilty of the body and blood of the Lord. But let a man examine himself, and so let him eat of that bread, and drink of that cup. 29 For he that eats and drinks unworthily, eats and drinks damnation to himself, not discerning the Lord’s body.” (1 Corinthians 11:27-28) Therefore, we should receive the Eucharist with absolute faith that it is truly the body and blood of Jesus Christ, but also examine ourselves and fulfill the Sacrament of Confession so that we won’t be “guilty of the body and blood of the Lord.

5. ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን
MYSTERY OF RESURRUCTION


ትንሣኤ ማለት ምን ማለት ነው? ትንሣኤ ማለት ነፍስና ሥጋ ተለያይተው ከኖሩ በኋላ ሁለተኛ ተዋሕደው መነሣት ማለት ነው። ትንሣኤ ለምን ሆነ? ሰው የተፈጠረው ነፍስና ሥጋው  ሳይለያዩ  በሕይወት ለመኖር እንጂ ለሞት አልነበረም፤ እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና። ኗሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረትን ፈጥሮአልና የሰዎች ጥፋት ደስ አያሰኘውም። መፈጠራችን ለድኅነት ነውና ሕይወት የማታልፍ ስለሆነች ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እግዚአብሔር ለሞት አላደረገነምና ለሕይወት እንጂ ፩ተሰ ፭፥፱ ይለናል።

ሰው ግን ኃጢአትን በመሥራቱ ማለት የፈጣሪውን ትዕዛዝ በመተላለፉ በራሱ ላይ ሞትን አመጣ፤ ሞት ከእግዚአብሔር ተፈረደበት። በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአትን ወደ ዓለም እንደገባ በኃጢአትም ሞት ገባ እንዲሁም በሰው ላይ ሞት አለፈ ሁሉ በድሏልና። (ሮሜ ፭፥፪)

ለመቃብርም በዚህ ዓለም ግዛት አልነበረውም።  እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎች ግን በቃል ጠሩት ባልንጀራም አደረጉት በዚህም ጠፉ። (መጽሐፈ ጥበብ ፩፥፲፫) ኃጢአተኛው ሰው እንደ አጋንንት በድሎ አልቀረም። የፈጣሪውን ትዕዛዝ በማፍረሱ ተጸጸተና ማረኝ ሲል ፈጣሪውንም ለመነው፤ ፈጣሪውም ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆነለት። ሰው ኃጢአትን ሠርቶ የተፈረደበትንም ሞት ተቀብሎ (ሞቶ) ሰውን ከኃጢአቱ ፍርድ አዳነው። ሞትን አጥፍቶ ሕይወትን መለሰለት። ስለዚህ በተፈጠረበት በጥንት ሕይወቱ ለመኖር ለሰው ትንሣኤ ሆነለት (ተሰጠው)። ትንሣኤ ቀደም ብሎ በነቢያት ታውቆ ስለነበር ስለ ትንሣኤ የተናገሩት ነቢያት ብዙዎች ናቸው ።

ከብዙዎችም ነቢያት የጥቂቶቹን ቃል ስንጠቀስ ከምዕራፍና ቁጥራቸው ጋር በዚህ መስመር በተጠቀሱት መጻሕፍት ቀጥሎ ያለውን ቃል እናገኛለን።  (መዝ ፻፬፥፴ ኢሳ ፳፮፥፲፱፤  ዳን ፲፪፥፪) እስትንፋስን ትልካለህ ይፈጠራሉም፤ የምድሪቱንም ፊት ታድሳለህ። ሙታንም ሕያዋን ይሆናሉ፣ ሬሶችም ይነሣሉ። በመሬትም  የምትኖሩ ተነሡ አመስግኑ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና። ምድርም ሙታንን ታወጣለች በምድርም መሬትም ያንቀላፉ ብዙ ሰዎች  ይነቃሉ እኩሌቶች ወደዘለዓለም ሕይወት ሌሎችም ወደ ስድብና ወደዘላለም ኃፍረት። ከነቢያትም ቃል በላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ አታድንቁ በመቃብር ያሉት ሁሉ ቃሉን የሚሰሙበት ግዜ ትመጣለችና ቃሉንም ሰምተው መልካም የሠሩ ወደ ሕይወት ትንሣኤ ይወጣሉ፤ ክፉም የሠሩ ወደ ፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ ሲል ትንሣኤ ሙታን እንዳለ አስረድቷል። (ዮሐ ፳፰፥፳፱)

ትንሣኤም ለሰው ዘር ሁሉ ነው ማለት ለጻድቃንም ለኃጥአንም ሁሉ ነው ። ትንሣኤ ሙታን መቼ ነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ዓለምን ለማሳለፍ ወደ ደብረ ጽዮን ይመጣል (ራዕ ፲፬፥፩) ሲመጣም ቀድሞ በዘመነ ሥጋዌው መጥቶ ሳለ በትህትና ይታይ እንደነበረ አይደለም፤ መላእክቱን አስከትሎ በግርማ መንግሥቱ  (በጌትነት ክብሩ)  በገሐድ ተገልጦ ይመጣል ማቴ ፲፮፥፳፯። የሙታን ትንሣኤ ጌታችን በሚመጣበት ጊዜ ነው። ትንሣኤ ሙታን እንደምን ነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጣ መላዕክትን  የመለከት ድምፅ እንዲያሰሙ ያዛቸዋል። መላእክት ሦስት ግዜ የመለከትን ድምፅ ያሰማሉ ።

የመጀመሪያው የመለከት ድምፅ በተሰማ ግዜ የዱር አውሬ፣ የባሕር አዞ ጉማሬ የበላው፣ ባሕር ያሰጠመው ፣ በእሳት የተቃጠለው ፣ በመቃብር የተቀበረው ሁሉ ሥጋ ራሱ ከወደቀበት ይሰበሰባል። ሁለተኛው የመለከት ድምፅ በተሰማ ጊዜ የተሰበሰበው የሰው ሥጋ ከራሱ ጀምሮ ይያያዝና ምሉዕ አካል ይሆናል። ሦስተኛው የመለከት ድምፅ በተሰማ ጊዜ ነፍስ ካለችበት መጥታ ተዋሕዳው ሕያው ሆኖ ፈጥኖ ይነሣል። (፩ቆር ፲፭፤ ፶፪) የመለከት ድምፅ የተባለው ምሳሌ ነው። እውነቱ ግን የጌታ ትዕዛዝ ነው። የምድር ንጉሥ ክተት ሲል ነጋሪት ያስጎስማል፣ መለከት ያስነፋል። ይህን ግዜ ሠራዊቱ ሁሉ በአንድ ጊዜ ይከታል።

የጌታም ትዕዛዝ ሁሉን የሚሰበስብ ስለሆነ በመለከት ድምፅ ተመስሏል። ትዕዛዙም “ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም”  ማለትም «የሞት እንቅልፍ ያንቀላፋህ ሟች ሁሉ ንቃ፤ ተነሣ» የሚል ነው። ይህንን ትዕዛዝ የሚያሰማው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነው። ይህን ሲነግረን እርሱ ጌታ በዕልልታ በመላዕክት አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአንደኛ ተሰሎንቄ መልእክቱ በምእራፍ አራት ቁጥር አሥራ ስድስት ላይ ይነግረናል።  የመለከት ድምፅ በተሰማ ግዜ ይነሣል የተባለው የሞት እንቅልፍ ያንቀላፋህ ሟች ተነሣ የሚል ትዕዛዝ በተነገረ ግዜ ፈጥኖ ይነሣል ማለት ነው። ከሞት ድነን ስንነሣም በጎም ሆነ ክፉ ዛሬ ሰውረን የሠራነው ያን ጊዜ  ይገለጣል፤ ገልጸን የሠራነው ይነገራል።

  • ያን ጊዜ መላእክት ኃጥአንን ከፃድቃን ይለዩአቸዋል (ማቴ ፲፫፥፵፱)
  • ያን ጊዜ ኃጥአን ጠቁረው ይታያሉ፤ ፃድቃን እንደ ፀሐይ በርተው ይታያሉ (ማቴ፲፫፥፵፪)
  • ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓርብ ዕለት በመስቅለ እንደተሰቀለ እጁንና እግሩን እንደተቸነከረ ሆኖ ይታያል።

ስለምን? ቢባል “ለእናንተ ስል ይህን መከራ ተቀበልኩ ብሎ ፍቅሩን ለሰው ለማስታወስ፤ ላድናችሁ ብመጣ የሰቀላችሁኝ፣ የዘበታችሁብኝ እኔ ነኝ” ብሎ የሰቀሉትን፣ ሐዋርያት መምሕራን ተሰቀለ፣ ሞቶ፣ ዓለምን አዳነ ብለው ቢያስተምሯችሁ “አናምንም አንቀበልም” አላችሁኝ እኔ ነኝ ብሎ የኋላ ከሃድያንን ለመውቀስ ነው።

እንዲህ ሆኖ ባዩትም ጊዜ አስቀድመው የሰቀሉትና በችንካር የወጉት ያለቅሳሉ (ራእ ፩፥፯)

  • ያን ጊዜ ፃድቃን በበጎ ምግባራቸው ይመሰገናሉ (ማቴ ፳፭ ፤፵፩ )
  • ያን ግዜምኃጥአን  ያለቅሳሉ (ማቴ ፳፬፥፴)
  • ያን ጊዜም ሁሉም እንደ ሥራው ተገቢውን ይቀበላል ማለት ፃድቃን የበጎ ምግባራቸውን ዋጋ ኃጥአንም የክፉ ምግባራቸውን ፍርድ ይቀበላሉ። (፪ቆሮ ፭፥፲፣ ሮሜ ፪፥፲፮ ፣ራእ ፳፥፲፪)

ያን ግዜ ኃጥአን ወደ ዘላለም ስቃይ ይሄዳሉ፤ ፃድቃንም  ወደዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ። ማቴ ፳፭፥፵፮ ከዚህ በኋላም ሰማይና ምድር ያልፋሉ ፣ መላዕክትና ሰዎች ይቀራሉ (ማቴ ፳፬፥፴፭) ከዚህም በኋላ ኃጥአንና አጋንንት ከአለቃቸው ከዲያቢሎስ ጋር በስቃይና በዋይታ በገሃነም  ይኖራሉ።

መላእክትና ፃድቃንም ከጌታቻው ከክርስቶስ በዕረፍትና በደስታ በመንግሥተ ሰማይ ይኖራሉ። ጌታችን የሚመጣው መቼ ነው?  ጌታ የሚመጣበት ዘመኑና ጊዜው አይታወቅም (ማቴ ፳፬፥፴፯)

ዕለቲቱ ግን ዓለም የተፈጠረባት እሑድ እኩለ ሌሊት ናት (ሉቃ ፩፥፴፩;፤ ማቴ ፳፰፥፩-፭)

Resurrection is the Mystery of life after death. All those who have departed since the time of Adam until the second coming of Christ, at which point they will be raised in the union of body and soul. The souls of the righteous shall abide in Paradise and the souls of sinners in Hades until the end of this world but on the last day, when our Lord and savior Jesus Christ shall come in His glory, to judge the living and the dead, the souls shall be united with their bodies on the day of resurrection and they shall rise from the dust of the earth. (Lk. 16:19-31).

"Marvel not at this: for the hour is coming; in which all that are in the graves shall hear his voice and shall come forth; they that have done good, unto the resurrection of life; and they that have done evil, unto the resurrection of damnation." (Jn. 5:28). 

"The dead men shall live. Together with my dead body shall they arise. Awake and sing, ye that dwell in dust: for they dew is as the dew of herbs, and the earth shall cast out the dead." (Is. 26:19-20).

Daniel the prophet has written ". . . and at that time thy people shall be delivered, everyone that shall be found written in the book. And many of them that sleep in the dust of the earth shall awake, some to shame and everlasting contempt. And they that be wise shall shine as the brightness of the firmament; and they that turn many to righteousness as the stars forever and ever.” (Dan. 12:1-3). Job said "for I know that my redeemer liveth, and that he shall stand at the latter day, upon the earth: And though after my skin worms destroy this body, yet in my flesh shall I see God: whom I shall see for myself and mine eyes shall behold, and not another," (Job. 19:25-27)

The Bible also teaches us about the prophet Elijah and his disciple Elisha who raised the dead. (1Kgs. 17:21; 2Kgs. 13:21). Jesus Christ the Lord, and his disciples raised the dead in their ministry while proclaiming the Gospel. (Mt. 9:25; Lk. 7:15; Jn. 11:14). Likewise, the Apostles also raised the dead during their apostolic ministry. 

On the day of the crucifixion of our Lord Jesus Christ, the graves were opened and bodies of many saints came out. (Mt. 27:52). All those that sleep in the dust of the earth shall come to life at the last judgment. Our belief in our resurrection is based on the resurrection of Christ. "Knowing that He which raised up the Lord Jesus shall raise up us also by Jesus, and shall present us with you." (2Cor. 4:14). 

Resurrection is for all human beings. Both the righteous and unrighteous will arise. The final resurrection waits the last day at the second coming of our Lord and Savior Jesus Christ. Our Lord and Savior Jesus Christ shall come in His glory at the end of the world to judge the living and the dead. (Ps. 50:2; Mt. 25:31-32; Rev. 1:7). 

At that time, He shall send forth His angels with a great sound of a trumpet. The dead shall arise. The earth will restore that which was entrusted to it. Then He shall set the righteous on his right hand and the sinners on the left hand. All arise carrying their works, which followed them from the Earth; the righteous will be sanctified with the word of blessing, but the sinners will be rebuked with the word of accusation. The righteous shall shine as the sun, and inherit the kingdom following Christ, while the sinners shall go away into everlasting punishment prepared for the devil and his angels. (Mt. 13:42-49; 25:31-43; 2Cor 5:10; Rev. 20:12).