Niseha-1
ንስሐ
PENANCE
ንስሐ መግባት ማለት መጸጸት፣ ከኃጢአት ይቅርታ መጠየቅ እና መንፈሳዊ
መታደስን ማግኘት ማለት ነው። ምንም እንኳን ክርስቲያኖች በጥምቀት
ዳግመኛ ቢወለዱም ሰው ፍጹም ስላልሆነ ኃጢአት ይሠራል። ስለዚህ
ማንኛውም ክርስቲያን የነፍስ አባት ሊኖረው ይገባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኃይማኖት ተከታዮች ወደ
ንስሐ አባታቸው በመሄድ ኃጢአታቸውን ሊናዘዙ ይገባል። (1ኛ የየሐንስ መ.
ም.1 8-10፣ ዘሌ. 14:31፣ ማቴ. 8:4፣ ሃይማኖተ አበው 59:20)።

ከልብ በመነጨ ንስሐ (መጸጸት) ምህረትን ለማግኘት ቀኖናን በመቀበል
ምዕመናን በእግዚአብሔር ምህረት እና ጸጋ እፎይታ እና መጽናናትን ያገኛሉ፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታቸውም ይጎለብታሉ።

The word "Penance" means to feel remorse and
repent, seeking forgiveness from sin and attain
spiritual renewal. Although Christians are reborn
through Baptism, human beings are liable to
commit sins. Therefore, every Christian should
have a father confessor (Nesha Abbat).

Followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo
Church should go to the father confessor and
confess their sins. (Lev. 14:31, Mt. 8:4; Epiphanius
Faith of Fathers (Haimanot Abew) 59:20).

Through heartfelt remorse and the receiving of
absolution, believers find solace in the assurance
of God’s mercy and grace, fostering a deeper
spiritual connection within the Ethiopian
Orthodox faith community.