
በመካነ ብርሃን የእሁድ የማለዳ ፀሎት በ5፡00 ሰዓት ይጀምራል።
በመጀመሪያ መልክአ ስዕል ይደርሳል፡፡ በመቀጠል መቅድም እና ታምረ ማርያም
(የድንግል ማርያም የተአምራት መጽሐፍ) ንባብ አለ። ከዚያም ድርሳነ
ሚካኤል እና ዜና ሥላሴ ይነበባሉ።
ተአምረ ኢየሱስ (የኢየሱስ ተአምራት) በመጨረሻ ይነበባል።
ቀጥሎ ጸሎተ ኪዳን (የኪዳን ጸሎት) በዜማ እና በንባብ ይጸለያል።
ኪዳን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ለኃዋሪያት
ያስተማረው ሲሆን ከሰማንያ አሀዱ መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ኪዳን
ሁሉን ቻይ የሆነውን የብርሃን አምላክ ስላደረገልን ሁሉ
የምናመሰግንበት ጸሎት ነው። በዕለቱ የክርስትና ወይም
የቅዱስ ጋብቻ አገልግሎት ከሌለ ሥርዓተ ቅዳሴ ይከተላል።
እንዲሁም የእለቱ የቅዱስ ያሬድ መዝሙር በመሪጌቶች ይቆማል፡፡
The morning prayers on Sundays at Holy Trinity
EOTC begin at 5am. First, there is the reading of
“Tamire Mariam” (the book of the Miracles of Virgin
Mary), which is always followed by “Dirsane Michael”
(The Works of the Archangel Michael) and “Zena
Selassie (The Book of the Holy Trinity).
Then the books of saints that are commemorated
that day are read. “Tamire Iyesus” (Miracles of Jesus)
is then read last. After a few more prayers asking for
the Virgin Mary’s intercession, the last prayer is said,
Kidan (the Prayer of the Covenant).
Kidan is said to praise the almighty God who is full of
Light for all that he has given us. If there is no
baptism or Holy Matrimony service that day then
the day continues with the Divine Liturgy.
The day’s St. Yared “Mezmur” (Chants) are recited by
the cantors of the parish.