service_7
ጋብቻ ፤ ሥርዓተ ተክሊል
MATRIMONY
መካነ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትውፊት
መሠረት አንድ ወንድ በአንዲት ሴት አንዲት ሴት በአንድ ወንድ ጸንተው
እነዲኖሩ የተቀደሰ ጋብቻን ትፈጽማለች። የትዳር ጓደኞች በካህናቶቻችን
እየተመሩ በቅዱስ ቁርባን ጋብቻ ውስጥ አንድ የሚያደርጋቸውን መንፈሳዊ
ጉዞ ይጀምራሉ። በቤተ ክርስቲያኒቱ በረከትና በማኅበረሰቡ ድጋፍ
እያንዳንዱ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን የተከበረው የፍቅር፣ የቁርጠኝነት እና ዘመን የማይሽረው
እሴት ነው።

ሥላሴ የመታጪያ ወርቁን ለመላእክት ሰጡ መላእክት ለአዳዳም ሰጡ
አዳምም ንስኢ እጼኪ መታጪያሽን እንቺ ብሎ ለሔዋን ሰጥቶ ጋብቻን
መስርቷል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት
በማለት ጋብቻቸውን ባርኳል፡፡ (ኦሪት ዘፍ. ም.1 ቁ.27-29 )

"እግዚአብሔር አምላክም አለ፡ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም
አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።" (ዘፍ 2: 18)

ማሳሰቢያ: መካነ ብርኃን ቅድስት ሥላሴ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በየጊዜው
ለምእመናን ሃይማኖታዊ የጋብቻ ሥርዓት አገልግሎት ትሰጣለች። ይህንን
አገልግሎት ለማግኘት ተጋቢዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

Our matrimony services honor the sacred union of
marriage in the Ethiopian Orthodox Tewahedo tradition
between one man and one woman. Guided by our
clergy, couples embark on a spiritual journey that
unites them in the holy sacrament of matrimony. With
the blessings of the church and the support of the
community, each marriage ceremony is a cherished
celebration of love, commitment, and the timeless
values upheld by the Ethiopian Orthodox Church.

God, as a father and a mother, blessed Adam and
Eve with marriage accompanied by angels. Marriage
is not established by man's own will and wisdom,
but it is established by God's wisdom and will.
(Gen. 1: 27-29)

"The LORD God said, “It is not good for the man
to be alone. I will make a helper suitable for him."
(Gen 2:18)

Holy Trinity EOTC provides holy matrimony services
for its members. Membership to the church is mandatory
to receive this service.