CREED OF OUR FAITH
ጸሎተ ሃይማኖት
1.
We believe in one God, Father Almighty,
Creator of heaven and earth, and of all
things visible and invisible.

(Gen. 1:1-28; Neh. 9:6-7; Rom 1.20-21; Is 48:12-13)
፩- ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን
በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።

(ዘፍ. 1፡1-28፤ ነህ. 9፡6-7፤ ሮሜ 1፡20-21፤ ኢሳ 48፡12-13)
2.
And in one Lord Jesus Christ, the
only-begotten Son of God, begotten of the Father
before all ages;

(John. 3:16; 1 Cor. 8:6; Heb. 1:5; John 8: 31; John 17:5)
፪- ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ
በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን።

(ዮሐ 3:16፣ 1 ቈሮ. 8:6፣ ዕብ. 1:5፣ ዮሃ. 8:31፣ ዮሃ. 17:5)
3.
Light of Light, true God of true God,
begotten, not created, of one essence with
the Father through Whom all things were made.

(John 1: 1-4; John 10:30; John 14:9; John 16:28)
፫- ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ
አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር
የሚተካከል።

(ዮሐ 1:1-4፤ ዮሐንስ 10:30፤ ዮሐ 14:9፤ ዮሐ 16:28)
4.
There is nothing in heaven and earth which
exists without Him.

(John 1:3; Col. 1:16)
፬- ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤
በሰማይም ያለ በምድርም ያለ።

(ዮሐ 1:3፣ ቈሎ. 1:16 )
5.
Who for us men and for our salvation came
down from heaven and was incarnate of the
Holy Spirit and the Virgin Mary and became man.

(Luke. 1: 33-34; Is 7:14; Matt 1:18; Gal 4:4)
፭- ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማየ ሰማያት ወረደ።
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።

(ሉቃ. 1:33-34፣ ኢሳ. 7:14፣ ማቴ 1:18፣ ገላ 4:4)
6.
He was crucified for us under Pontius Pilate,
and suffered and was buried; And He rose on
the third day, according to the Scriptures

(Matt 27:24-26; Matt 27:49; Luke 24:5; 1Cor 15: 20-21)
፮- ሰው ሆኖ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤
ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን
ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ።

(ማቴ27:24-26፣ ማቴ 27:49፣ ሉቃ 24:5፣ 1 ቈሮ. 15:20-21)
7.
He ascended into heaven and is seated at
the right hand of the Father; And He will
come again with glory to judge the living
and dead. His kingdom shall have no end.

(I Pet. 3: 18; Phil. 2: 6-8; Rom. 5: 8; Cor. 15: 3-4; 1 Pet. 3: 19-20.)
፯- በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።
ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል።
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።

(1 ጴጥ. 3:18፣ ፊል. 2:6-8፣ ሮሜ 5:8፣ ቈረ. 15:3-4፣ 1 ጴጥ. 3:⁠19-20)
8.
And in the Holy Spirit, the Lord, the Creator
of life, Who proceeds from the Father, Who
together with the Father and the Son is
worshipped and glorified, Who spoke
through the prophets.

(John. 5:17-19; John 14:15-18፤ John 15: 26; 2 Pet 1:21)
፰- ጌታ፤ ማኅየዊ በሚሆን ከአብ በሰረፀ በመንፈስ ቅዱስም
እናምናለን፤ እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና
ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ።

( ዮሃ. 5:17-19፣ ዮሃ. 14:15-18፣ ዮሃ. 15:26፣ 2 ጴጥ. 1:21
9.
In one, holy, universal, and apostolic Church,
formed through the assembly and
congregation of the Disciples

(Eph. 2: 19-22; Matt 16:18; Eph. 5:25; Matt 18:17)
፱- ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።

(ኤፌ. 2:19-22፣ ማቴ 16:18፣ ኤፌ. 5:25፣ ማቴ 18:17)
10.
We confess one baptism for the forgiveness of sins.
(Eph. 4: 3- 6 Ps32. 1-2; Eph. 1: 6; Mark 16:16; Acts 2:38)
፲- ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።
(ኤፌ. 4:3-6 መዝ. 32. 1-2፣ ኤፌ. 1:6፣ ማር. 16:16፣ የሐዋ ሥራ 2:38 )
11.
We look for the resurrection of the dead, and
the life of the age to come.

(John. 5:28 -29, 1 Cor. 15: 22- 24, John. 10: 27- 28.)
፲፩- የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን።

(ዮሐ. 5:28-29፣ 1 ቈረ. 15:22-24፣ ዮሐ.10:27-28 )
12.
And the life of the age to come.
(John. 17:3)
፲፪- የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ።
(ዮሐ. 17:3)

 

Amen

 

አሜን።