sibket-
ስብከተ ወንጌል
BIBLICAL TEACHING

"እንዲህም አላቸው ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ
ያመነ የተጠመቀም ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል" (ማር 16፡15 -16)

"ወንጌል" የሚለው ቃል "ዩአንጌሊዎን" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው
በግእዙ ቋንቋ ብሥራት ይባላል፡፡ የግሪኩም ይሁን የግእዙ ትርጉም
የምሥራች ማለት ነው፡፡

ወንጌል በሚል ቃል የተጠራው የመድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዜና
ልደቱና ትምህርቱ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ትምህርት የሠራው
የአድኅኖት ሥራ ሁሉ ወንጌል ተብሏል፡፡

ወንጌል ከላይ እንዳየነው የምሥራች ሲሆን ልዑል አምላክ ከቅድስት ድንግል
ማርያም በግብረ መንፈስ ቅዱስ መወለዱን በሞቱ ዓለምን ማዳኑን
ስለሚያበሥር ነው፡፡

ዘወትር ከሥርዓተ ቅዳሴ መርሃግብር በኋላ ተአምረ ማርያም ይነበባል፣
ለሕፃናት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርተ ወንጌል ይሰጣል፣እንዲሁም በእለቱ
በተመደቡት መምህር ለምእመናን ወንጌል ይሰበካል። በተጨማሪም
በየሳምንቱ ዓርብ ከ6፡00 PM ጀምሮ የጸሎት እና የስብከተ ወንጌል
አገልግሎት ይሰጣል።

"And he said to them, 'Go into all the world and
preach the gospel to every creature. He who
believes and is baptized will be saved.’” (Mark 16:15)

The word "Gospel" comes from the Greek word
"Euangelion" which is called Bisrat in the Geez
language. The meaning of Greek or Geese means good news.

The Gospel is the news of our savior Jesus Christ's
birth and teaching. All the salvation work that Jesus
Christ taught and did is called the Gospel.

As described above, the Gospel is good news
because it announces the birth of the Most High
God from the Holy Virgin Mary through the Holy Spirit.

Holy Trinity will preach the gospel after every
celebration of the Divine Liturgy and the reading of
the Miracles of the Virgin Mary. This includes a brief
English sermon for the youth and children, followed
by Bible teaching by the assigned member of the
clergy for the day.

We also have weekly Bible study every Friday
starting at 6:00 PM.