service_4
ጥምቀተ ክርስትና
BAPTISM
"ጥምቀት" የሚለው ቃል በቀጥታ ሲተረጎም በውሃ ውስጥ መጥለቅ
ማለት ነው። እሱ ለአሮጌው ሕይወት መሞትን እና ወደ አዲስ የሕይወት
መንገድ የመወለድን አዲስ ጅምር ያሳያል።

በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰው መጥምቁ ዮሐንስ ሕዝቡን
ሲያጠምቅ ዓለምን ለማዳንና ለመጪው የእግዚአብሔር መንግሥት
ለማዘጋጀት የዮሐንስ ጥምቀት የንስሐ ምልክት ሆኖ እናገኘዋለን።
ክርስቶስ ራሱ በዮሐንስ የተጠመቀው ጸጋ እና ክብር ለማግኘት ሳይሆን
ውሀዎችን ለመቀደስ ፣የእግዚአብሔር “የተወደደ ልጅ”፤ አዳኝና መሲሕ
መሆኑን ለመግለጽ ነበር። (ማቴ 3፣ ማርቆስ 1፣ ሉቃስ 3፣
ዮሐንስ 1-3)።

ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን እውነት በመቀበል ሰዎችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ልጆች ለማድረግ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሥም ታጠምቃለች።
በማቴዎስ መጽሐፍ እንደተጻፈው ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን
ሄደው ሕዝቡን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም
እንዲያጠምቁና ደቀ መዛሙር እንዲያደርጓቸው አዘዛቸው (ማቴ
28፡19-20)። ይህንን በማሰብ ቤተክርስቲያን ሁሉንም ታጠምቃለች፤
እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅነትንም ታሰጣለች። በዚህም መሰረት
ወንዶች ልጆች በተወለዱ በ40ኛው ቀን፣ ሴቶች ልጆች ደግሞ በተወለዱ
በ80ኛው ቀን መጠመቅ አለባቸው (ዘሌዋውያን 12፤ 1-መጨረሻው፡)

የክርስትና ወረቀት ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

The term "Baptism" literally means the immersion in
water. It symbolizes a new beginning, of dying to an old,
way of life and being born again into a new way of life.

In the Gospels we find John the Baptist baptizing the
people as a sign of repentance in preparation for the
Kingdom of God which was coming to men with Christ
the Messiah. Christ himself was baptized by John not
because he was sinful and needed to repent, but
because in allowing himself to be baptized he showed
that indeed he was God’s “Beloved Son,” the Savior and
Messiah, the “Lamb of God who takes upon himself the
sins of the world” (Matt 3, Mark 1, Luke 3, John 1–3).

By accepting this truth, our Church baptizes people in
the name of the Father, the Son, and the Holly Spirit in
order to make them Children of Jesus Christ. In the book
of Mathew, Jesus Christ told his disciples to go and
baptize all the people in the name of the Father, the Son,
and the Holly Spirit and make them his disciples
Mathew 28:19). For this reason, the Church baptizes
everyone and makes him or her true Child of God. Boys
have to be baptized on the 40th day of their birth while
girls have to be baptized on the 80th day (Leviticus 12).

To request a Baptism Certificate, click here